የሀገር ውስጥ ዜና

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚገኘውን የእድገት በስራ ሁለገብ የሸማኔዎች የህብረት ስራ ማህበር ጎብኙ

By Tibebu Kebede

May 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ መርካቶ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚገኘውን የእድገት በስራ ሁለገብ የሸማኔዎች የህብረት ስራ ማህበር ጎብኙ።

የህብረት ስራ ማህበሩ በ19 67 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን፥ ሰራተኞቹ በአብዛኛው አረጋውያን ናቸው፡፡

የማህበሩ አባላት የሚሰሩበት ሁኔታ አመቺ ባይሆንም ስራቸውን በከፍተኛ ሞራል እና ትጋት እየሰሩ በአክሲዮን ተደራጅተው በዘመናዊ መልክ እንዲሰሩ ድጋፍ መጠየቃቸውን ወይዘሮ አዳነች አስታውቀዋል፡፡

ወይዘሮ አዳነች ለማህበሩ አባላት ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እደሚሰጡም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!