አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዓለም አቀፍ ሪፐብሊካን ኢንስቲቲዩት (IRI) ለዓለም አቀፍ የዴሞክራቲክ ኢንስቲቲዮት (NDI) የምርጫ ታዛቢ ቡድን የምርጫ መታዘብ እውቅና መስጠቱን አስታውቋል።
ቦርዱ የድርጅቶቹ የጋራ የታዛቢ ቡድን ያቀረበውን የጥናት ዘዴ በማየት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች መሰረታዊ መርሆዎችን እና የታዛቢዎች ዓለም አቀፍ የስነምግባር ደንብን በተከተለ መልኩ እንደሚሰሩ ስምምነት ላይ በመድረስ የመታዘብ እውቅናውን መስጠቱን ገልጿል፡፡
በዓለም አቀፉ የኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የታዛቢ ቡድኑ የሚያከናውነው የመታዘብ ተግባር የስፋት ውስንነት እንደሚኖረውና ይህንንም በሚያደርጋቸው ስራዎች እና ማጠቃለያዎች ላይ የሚገለጽ መሆኑን ታዛቢ ቡድኑ እና ቦርዱ በጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ቦርዱ ከዚህ በፊት ለ45 የሃገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች እውቅና መስጠቱ ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!