Fana: At a Speed of Life!

ለጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች እገዛ የሚውል የ21 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወተር ዊትነስ ኢንተርናሽናል ከተባለ የልማት ድርጅት ጋር በኢትዮጵያ ለሚገኙ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች እገዛ የሚውል የ21 ሚሊየን 72 ሺህ 26 ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

በሚኒስቴሩ የቆዳና ጨርቃጨርቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አበበ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ለማድረግ ያሳየው ተነሳሽነት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡

የአግሮ-ፕርሰሲንግና ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አማካሪ አቶ ጳውሎስ በርጋ በበኩላቸው ሀገሪቱ ለምትከተለው የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ የውሃ ሀብትን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ለዚህ ተግባራዊነትም የዛሬው ስምምነት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የወተር ዊትነስ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ኢሳያስ ሳሙኤል የፕሮጀክቱ ተቀዳሚ ዓላማ በሀገሪቱ የሚገኙ የጨርቃጨርቅናአልባሳት ኢንዱስትሪዎች በተለይም በውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ያለባቸውን ክፍተት መሙላት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ለዚሁ ዓላማ 500 ሺህ ፓውንድ ተመድቧል ያሉት አቶ ኢሳያስ ዓላማውን ለማሳካት ድርጅቱ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተጓዳኝ ከሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ይሰራል ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.