የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የበረራ አየር ክልል ሽፋኗን 97 በመቶ ማድረሷ ተገለጸ

By Meseret Awoke

May 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኢትዮጵያ የበረራ አየር ክልል ሽፋን 97 በመቶ መድረስ መቻሉን አስታወቀ።

ኢትዮጵያ የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀሟ ለአየር ትራንስፖርት ደህንነት መጠበቅ የራሱን አሰተዋጽኦ እየደረገ እንደሚገኝ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ የኢትዮጵያን የአየር ክልል ትራፊክ ከመቆጣጠር አልፎ የሌሎች የጎረቤት ሀገሮችንም ጭምር እየተቆጣጠረ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ተቋሙ በአቪዬሽን ስልጠና ዘርፍም ከሀገር ውስጥ ስልጠና አልፎ የውጭ ሀገር ዜጎችን በብቃት በማሰልጠን የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!