የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ የአፍሪካ ቀንን አስመልክተው መልዕክት አስተላለፉ

By Meseret Awoke

May 25, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ቀንን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም የበለጸገች ሀገር ለመገንባት የሚደረገው ጉዞ በራሱ ፈታኝ ነው፥ ሆኖም በታላቁ አትሌት አበበ ቢቂላ በተግባር እንዳየነው ምቹ የሚባለው መንገድ እንኳ ባዶ እግርን ያቆስላል ብለዋል፡፡

የጉዞውን ስኬታማነት ራዕይን አጥርቶ በማየት እና በ“ባዶ እግርም” ቢሆን ጎዳናውን ሳይለቁ በመገስገስ ይወሰናል ሲሉም በፌስቡክ ገጻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!