አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)44 ሚሊየን 737 ሺህ 757ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ልዩ ልዩ የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት በተለያዩ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎችና ኬላዎች መሆኑ ተመላክቷል።
ከዚህ ውስጥ 43 ሚሊየን 131 ሺህ 467 ብር የሚገመቱት ወደ ሀገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ሲሆኑ÷ 1 ሚሊየን 606 ሺህ 290 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ደግሞ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር የተያዙ ናቸው፡፡
በዕቃ ዓይነት 9 ሚሊየን 396 ሺህ 655 ብር የሚገመት መደኃኒት ጨምሮ የምግብ ምርቶች፣ ሲጋራ፣ ኮስሞቲክስ ዋና ዋና የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የሚገኙበት መሆኑ ተመላክቷል።
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በፍተሻ፣ በበረራ እና በጥቆማ የተያዙ ሲሆኑ ዕቃዎቹን ሲያጓጉዙ የተገኙ 32 ተሽከርካሪዎች ከዕቃዎቹ ጋር መያዛቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!