የሀገር ውስጥ ዜና

ብሔራዊ ክብር በሕብር” መርሐ ግብር በተለያዩ አከባቢዎች  ተካሄደ

By Feven Bishaw

May 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ብሔራዊ ክብር በሕብር” በሚል ሀሳብ በታዋቂ ኢትዮጵያውያን የተጀመረው ንቅናቄ በተለያዩ አከባቢዎች  ተካሄዷል፡፡

ንቅናቄው በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች ሲካሄድ እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ፣ዛሬም እንደትናንቱ ሉዓላዊት ሃገር እናስቀጥላለን ፣ግድባችን ይሞላል ኢትዮጵያ ትቀየራለች፣በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ጣልቃ አትግቡ፣ሉዓላዊነታችንን አክብሩ የሚሉና ሌሎች መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡