የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነችና የቀድሞው ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለበከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

By Tibebu Kebede

May 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከቀድሞው ምክትል ከንቲባ እና የማዕድን እና ነዳጅ ሚንስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን የ1 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ታላቁ ቤተ መጽሀፍት ግንባታና የማዘጋጃ ቤት እድሳትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ሀገር በመሪዎች ቅብብሎሽ ፣ መልካም ጅማሬዎችን በማስቀጠልና ጎዶሎዎችን በመሙላት ትገነባለች ያሉት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የጀመረውን እኛ አስቀጠልን ፤ ዛሬ በመጠናቀቅ ደረጃ ላይ አድርሰናል ብለዋል።

በዚህ የቅብብሎሽ ስራ ብልጽግና መጀመርም ፣ መጨረስም ይችላል ብለዋል፡፡

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር እና የቀድሞ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው ያለእረፍትና በከፍተኛ ልፋት የተሰራ ስራን ውጤት ማየት ልዩ ደስታን ይሰጣል ሲሉ መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሪታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዛሬው እለትም የማዘጋጃ ቤት መልሶ እድሳትና ግዙፉን ሸገር ቤተ መፃህፍት ፕሮጀክቶች የደረሱበት ደረጃ እጅግ የሚያስደንቅ ነው ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!