የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከክልል አመራሮች ጋር የሚያደርጉት ውይይት ተጀመረ

By Meseret Awoke

May 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቀጣይ 3ወራት ተግባራት ዙሪያ ከክልል አመራሮች ጋር የሚያደርጉት ውይይት ተጀምሯል፡፡

በሀገራዊ ጉዳዮች እና በቀጠና ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና ከክልል አመራሮች ጋር የሚካሄድ የሁለት ቀናት ስብሰባ ዛሬ መጀመሩን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስብሰባው መንግሥት በቀጣይ ሦስት ወራት የሚያከናውናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለመወያየት እና ዕቅድ ለማውጣት ያለመ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!