የሀገር ውስጥ ዜና

መርካቶ ዘመናዊ የከተማ አውቶቡስ ተርሚናል ተመረቀ

By Tibebu Kebede

May 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ200 ሚሊየን ብር የተገነባው መርካቶ ዘመናዊ የከተማ አውቶቡስ ተርሚናል ተመርቋል።

ተርሚናሉ በአንድ ጊዜ ለ20 አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሲሆን የራሳቸው መግቢያና መውጫ ያላቸው ሁለት ወለሎችም አሉት።

35 የሚደርሱ የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅት መስመሮች እና 17 የሚሆኑ ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት መስመሮች በድምሩ 52 መስመሮች ላይ አገልግሎት መስጠት ያስችላልም ተብሏል።

በሰዓት ከ6 ሺህ በላይ በቀን ደግሞ እስከ 80 ሺህ የብዙሃን ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች አገልግሎት ይሰጣል።

በሜሮን ሙሉጌታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!