የሀገር ውስጥ ዜና

በህንድ የተከሰተው የኮቪድ19 ዝርያ አሳሳሳቢ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል – የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት

By Meseret Awoke

May 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ የተከሰተው የኮቪድ19 ዝርያ አሳሳሳቢ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አሳሰበ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በህንድ የተከሰተው የኮቪድ19 ቫይረስ አሳሳሳቢ ዝርያ እንደሆነ እና ዓለም አቀፍ ስጋት እየሆነ እንደመጣ ቫይረሱ እስካሁን በ44 ሃገራት እንደተሰራጨ ገልጿል።

ስለሆነም ሁሉም የህብርተሰብ ክፍል ለኮቪድ19 አጋላጭ ሁኔታዎችን በማስቀረት የመከላከያ መንገዶችን በጥንቃቄ እንዲተገብር ማሳሰቡንም ከኢንስቲቲዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!