ኮሮናቫይረስ

የኮቪድ-19 ምላሽ ሰጪ ሰራተኞች የኢድ አልፈጥር በዓልን በስራ ላይ አከበሩ

By Abrham Fekede

May 13, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ-19 ምላሽ ሰጪ ሰራተኞች 1 ሺህ 442ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓልን በስራ ላይ አከበሩ፡፡

በበዓል አከባበሩ ላይ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኮቪድ-19 ምላሽ ዋና አስተባባሪ አቶ አስቻለው አባይነህ ጨምሮ ሌሎች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

አቶ አስቻለው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኮቪድ-19 ቫይረስ መከላከልና ምላሽ ስራዎች ላይ ለተሰማሩ ባለሞያዎችና ለድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የኮቪድ-19 የመከላከል እና የምላሽ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንደሚያስፈልግ መግለጹን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!