Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በህንድ በኮቪድ 19 ምክንያት በሁለት ቀናት ውስጥ ከስምንት ሺህ ሰው በላይ ለህልፈት ተዳረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ በኮቪድ 19 ምክንያት በሁለት ቀናት ውስጥ ከስምንት ሺህ ሰው በላይ ለህልፈት ተዳርጓል፡፡

እንዲሁም ለአራት ተከታታይ ቀናት ደግሞ ከ400 ሺህ ሰው በላይ ቫይረሱ ተገኝቶበታል፡፡

በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ደግሞ ወረርሽኙ እየከፋ መምጣቱን ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡

በወረርሽኙ የሚጠቁ ሰዎች በምርመራ እጥረት ምክንያት ቁጥራቸው ከዚህ በላይም ሊያሻቅብ እንደሚችል ነው የተነገረው፡፡

የጤና ሚኒስቴሩ እንዳስታወቁት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ362 ሺህ ሰው በላይ ሲያዝ ባጠቃላይ ከ23 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ሰዎች ኮቪድ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በተጨማሪም 4 ሺህ 120 ሰው ሲሞት እስካሁን በሀገሪቱ 258 ሺህ 317 ዜጎቿ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎች እንደሚያነሱት ከሆነ ቁጥሩ ከአምስት እስከ አስር 10 እጥፍ እንደሚያሻቅብ ነው የሚጠቅሱት፡፡

ከ1 ነጥብ 35 ቢሊየን በላይ ህዝብ ያላት ህንድ እስካሁን 2 ነጥብ 8 በመቶ ዜጎቿን ብቻ ነው የከተበችው፡፡

በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ በወረርሽኙ ከሚያዙት ግማሽ ያህሉ ሰዎች ህንዳያውያን ሲሆኑ ለህልፈት ከሚዳረጉት ውስጥ ደግሞ 30 በመቶውን ቁጥር እንደሚይዙ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version