አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ700 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 42 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታቸው ተጠናቆ በተያዘው ዓመት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎቹ ግንባታ የሚገኝበትን ደረጃ ለቅዱስ ጊዮርጊስና ለኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎችና በተለያዩ አደረጃጀቶች ለሚገኙ ወጣቶች አስጎብኝቷል።
የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽነር በላይ ደጀን፥ “በከተማዋ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሆነባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በዚህ ዓመት ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ይሆናሉ” ብለዋል።
ወደ አገልግሎት ከሚገቡት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በግንባታ ላይ የነበሩና ገሚሶቹም በዚህ ዓመት የተጀመሩ እንደሚገኙበት ገልፀዋል።
ማዘውተሪያ ስፍራዎቹ የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና ሌሎች የስፖርት አይነቶችን ያካተቱ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!