አዲስ አበባ ፣ግንቦት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ )ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ10 ሺህ ሜትር የመጀመሪያ የውድድር ተሳትፎዋ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች፡፡
በፖርቹጋል በተደረገ የፌርናንዳ ሪቤይሮ ጎልድ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በመጀመሪያ ተሳትፎዋ 29 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ ከ42 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት አሸናፊ ሆናለች፡፡
ርቀቱን ያሸነፈችበት ሰዓት አትሌት አልማዝ አያና በሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ካስመዘገበችውና የዓለም ክብረ ወሰን ከሆነው 29 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ ከ45 ማይክሮ ሰከንድ በመቀጠል በኢትዮጵያ የርቀቱ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!