የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ፖሊሲና ማስፈፀሚያ ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

By Tibebu Kebede

May 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የአርብቶ አደር ፖሊሲና ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።

ፖሊሲና ማስፈጸሚያ ስትራቴጂውን የሰላም ሚኒስቴር ያዘጋጀው ሲሆን የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻልና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያስችላል ተብሏል።

የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ኑሮ ለማሻሻልና ለማዘመን እንዲቻል የተዘጋጀ እንደሆነ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ አልማዝ መሰለ፣ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን እና ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!