አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ አየር ሀይል በትግራይ ክልል በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና በተቋማዊ ሪፎርም መልካም አፈፃፀም ለነበራቸው ለከፍተኛ መኮንኖች ሹመት የምስጋናና እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር አካሄደ፡፡
በዚህም 44 ከፍተኛ መኮንኖች፣ 47 መስመራዊ መኮንኖች እና 985 ባለማእረግተኞች በድምሩ 1 ሺህ 79 የተፈቀደላቸውን ማእረግ የሚለብሱ ሲሆን 47 ከፍተኛ መኮንኖች ማእረጋቸውን ለብሰዋል፡፡
የአየር ሃይሉ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በአሁኑ ወቅት ከውጭና ከውስጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሀገሪቱን ለማፍረስ እየሰሩ ቢሆንም ዓላማቸው ግን እንደማይሳካ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
ይህን ለመመከትም አየር ኃይሉ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!