Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመዲናዋ የጋራ መኖርያ ቤቶች አካባቢ ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ የሚታዩ መጉላላቶችን ለመፍታት እርምጃ እንደሚወስድ ቦርዱ አስታወቀ

አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖርያ ቤቶች አካባቢ ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ የሚታዩ መጉላላቶችን ለመፍታት እርምጃ እንደሚወስድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ የነበረው ዝቅተኛ የመራጮች ምዝገባ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻል ከማሳየቱም በላይ መራጮች በተለይ የምዝገባው ማጠናቀቂያ ቀናት ሲቃረቡ በከፍተኛ ሁኔታ እየተመዘገቡ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ይህንን ተከትሎም በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖርያ ቤቶች አካባቢ ከፍተኛ ሰልፍ፣ የመራጮች ፍላጎት እና የምርጫ ጣቢያዎች አለመመጣጠን እንደተስተዋለ ጠቅሷል፡፡

በመሆኑም ካለፈው ሳምንት አንስቶ ቦርዱ በልዩ ሁኔታ ችግሩን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ገልጾ ይህንን ተከትሎ የሚወስዳቸውን እርምጃዎቹ እንደሚያሳውቅ ነው ያስታወቀው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለተፈጠረው የዜጎች መጉላላት ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን እርምጃዎቹን እስከሚያሳውቅ ዜጎች እና አስፈጻሚዎች በትእግስት እንዲጠብቁ ማሳሰቡን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version