የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ይበልጣል ከሱዳን ምሁራን ጋር ተወያዩ

By Abrham Fekede

May 06, 2021

አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳናውያን ምሁራን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ምሁራኑ ከካርቱም፣ ከአልኒሊን እና ከሱዳን ዩኒቨርስቲ የተውጣጣ የምሁራን ስብስብ ነው ተብሏል፡፡

ውይይቱ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካካል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ተግባራት ዙሪያ ትኩረት ማድረጉ ነው የተገለጸው፡፡

ከምሁራኑ ጋር የተደገረው ውይይት ከዚህ ቀደም ከዶክተር ኦመር አለሚን ጋር ከነበረው ቆይታ የቀጠለ ነው ተብሏል፡፡

ከምሁራኑ ጋር የተካሄደው ውይይት ከዚህ ቀደም የሁለቱ ሃገራት ምሁራን በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍንና በሕዝቦች መካከል ያለው ግንኙነት ለማጠናከር ተጨባጭ ሃሳቦችን ከማፍለቅና በመተግበር ረገድ ሊከናውኑ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከተደረገው ምክክር የቀጠለ መሆኑን በሱዳን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!