የሀገር ውስጥ ዜና

በደሴ ከተማ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርኃግብር ተካሄደ

By Meseret Demissu

May 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ማኅበር የተዘጋጀው ልዩ ”የአብረን እናፍጥር” የኢፍጣር መርኃግብር በደሴ ከተማ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ ተካሂዷል።

መርኃግብሩ ፍቅርንና አንድነትን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ መሆኑን የደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ማኅበር ሊቀመንበር ይማም አህመድ ተናግሯል።

በኢፍጣር ዝግጅት ላይ የደሴ ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብ፣  የክርስትና እምነት ተከታዮች እና አቅመ ደካሞች መታደማቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!