የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ጉብኝት አደረጉ

By Meseret Awoke

May 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ በኬሚካል ማምረቻ ዘርፍ፣ በማዕድንና የተለያዩ ዕቃዎች ማምረቻ ዘርፍ ፣ በጤፍ እርሻና ማቀነባበሪያ እና በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የተካተቱበት ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርጓል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሰማራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተመካክረዋል፡፡

በተጨማሪም የኩባንያዎቹ ተወካዮች በኢትዮጵያ ካሉ የግል ተቋማት ጋር ምክክር አድርገው በየዘርፎቻቸው የመስክ ጉብኝት ማካሄዳቸውን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!