Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኮቪድ-19 ምላሽ ሰጪ ሰራተኞች የፋሲካ በዓልን በስራ ላይ አከበሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ-19 ምላሽ ሰጪ ሰራተኞች የፋሲካ በዓልን በስራ ላይ አከበሩ፡፡

በዓሉ በስራ ላይ እያሉ እና በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ላጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው የተጀመረው፡፡

በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኮቪድ-19 ምላሽ ዋና አስተባባሪ አቶ አስቻለው አባይነህ ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም በማስተባበሪያ ማዕከሉ የቡድን አስተባባሪዎች እና ሌሎችም የክፍሉ ሰራተኞች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

ዋና አስተባባሪው የኮቪድ-19 ቫይረስ በኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ የኮቪድ-19 የመከላከልና የምላሽ ስራዎች መሰራታቸውንና ሊደርሱ የሚችሉ አስከፊ ችግሮችን መቀነስ መቻሉን ጠቅሰው ይህ እንዲሳካ ላደረጉ ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የኮቪድ-19 የመከላከል እና የምላሽ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ማሳሰባቸውንም ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version