አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የፋሲካ በዓልን በወይዘሮ ዘውዲቱ መሸሻ ብርሃን የህፃናት ማዕከል ከህፃናቱ እና ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር አከበሩ፡፡
በዓሉ የሰላም የጤናና የመተሳሰብ እንዲሆንና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች “እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በአል እንኳን አደረሳችሁ” ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ብርሃን የህጻናት ማሳደጊያን በ12 ሚሊየን ብር ወጪ ገንብቶ ለወይዘሮ ዘውዲቱ መሸሻ ያስረከበው መስከረም 22፣ 2012 እንደነበር ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!