አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ወደ ፕሪሚየር ሊግ በመግባቱ ከክልሉ መንግስት የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተለት።
ቡድኑ ቀሪ ጨዋታዎች እያሉት ከምድቡ አንደኛ በመሆን ፕሪሚየር ሊጉን መቀላቀል ችሏል።
ይህንን ተከትሎም የክልሉ መንግስት ለቡድኑ የ4 ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት ማበርከቱን እንዲሁም አሁን በፕሪሚየር ሊጉ እየተሳተፉ ለሚገኙት ሀዲያ ሆሳዕና ፣ ወላይታ ዲቻና ወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ቡድኖችም ለእያንዳዳቸው የ2 ሚሊየን ብር የማበረታቻ ስጦታ ማበርከቱን በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።
ለአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ቡድን የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን አስተዳደር አካላትና ደጋፊዎች ከሀዋሳ መግቢያ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።
ከክልሉ ፕሪሚየር ሊጉን በመቀላቀል አራተኛ የሆነው አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ከዚህ ቀደም በ2004 ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላቅሎ የነበረ ቢሆንም በ2010 ከሊጉ መውረዱ ይታወሳል።
በታምራት ቢሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!