የሀገር ውስጥ ዜና

የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ጎንደር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

By Tibebu Kebede

January 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ጎንደር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡

መነሻቸውን ጋሞ ያደረጉት የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች “ከጋሞ እስከ ጎንደር” በሚል መሪ ቃል ከ1 ሺህ 200 ኪሎ ሜትር በላይ የሰላም ጉዞ ካደረጉ በኋላ ዛሬ ረፋዱን ጎንደር ገብተዋል፡፡