Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደቡብ ክልል መንግስት ለ970 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል መንግስት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ970 የህግ ታራሚዎች ይቅርታና የእስር ዓመት ቅነሳ አደረገ ፡፡
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የትንሳዔ በዓልን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ህዝበ ክርስቲያኑ ቀጣዮቹን የስቅለትና የትንሳኤ በዓላት ሲያከብር ራሱን ከኮቪድ19 ለመከላከል በሚያችል መልኩ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግም በ23 የክልሉ ማረሚያ ተቋማት የነበሩ 970 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲለቀቁና የእስራት ቅነሳ እንዲደረግላቸው የክልሉ መንግስት መወሰኑን አቶ እርስቱ ገልጸዋል ።
ከእነዚህ የህግ ታራሚዎች ውስጥ 903 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ 52ቱ ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡
955ቱ ሙሉ ይቅርታ የተደረገላቸው እንደሆኑም ታውቋል።
ይቅርታ የተደረገላቸው ዜጎች ከእርምቱ ትምህርት ወስደው ወደ ሰላማዊ የህይወት መስመር እንዲመለሱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል ።
“እኛ ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የማይፈታ ችግር የለምና እርስ በርስ ልንደጋገፍ፣ ልንረዳዳና ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በጋራ ልንደግፍ ይገባል “ሲሉም መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version