አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 441 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመንገድ ጥገና ማከናወኑን አስታወቀ፡፡
ከተከናወኑት መካከልም 75 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ 24 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ጥገና፣ እንዲሁም 327 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ፅዳትና ጥገና፣ 11 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ሥራ እና የ16 ድልድዮች ጥገና ሥራ ይገኝበታል፡፡
በተለያዩ የጉዳት ምክንያቶች ከጥቅም ውጭ የሆኑ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቡ ክዳኖችን ለመቀየር በተደረገው ጥረት ከ3 ሺህ በላይ በማምረት የተሰበሩት ሲተኩ 4 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮብል ስቶን የጥገና ስራም ማከናወን ነው የጠቀሰው፡፡
የክረምቱ ወራት ከመግባቱ አስቀድሞም በተለያዩ የከተማዋ ማዕዘናት የሚገኙ ጥገና የሚያስፈልጋቸው ስፍራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው እንደሚሰሩ መገለጹን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!