የሀገር ውስጥ ዜና

134 የቀበሌ ቤቶች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች ተላለፉ

By Meseret Awoke

April 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)134 የቀበሌ ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎችና አቅመ ደካሞች ተላልፈዋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ 134 የቀበሌ ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎችና አቅመ ደካሞች ተላልፈዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ 134 የቀበሌ ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎችና አቅመ ደካሞች አስረክበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መንግስት የነዋሪዎችን ጥያቄ ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ያለውን ሃብት በመጠቀም ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማስፈን መጭውን ሃገር አቀፍ ምርጫ ዜጎች ንቁ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አባወይ ዮሃንስ በቤት እድል ፕሮግራሙ ተጠቃሚ የሆኑት ነዋሪዎች በብሎክ አደረጃጀት ጀምሮ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን በማስተቸትና በወረዳና በክፍለ ከተማ ካቢኔ በማጸደቅ የቤት እደላው መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የፋሲካ በዓልና እና ረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማው 10 ወረዳዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 1 ሺህ 236 ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!