አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 13 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 55 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ተደራሽቱን ለማስፋት ተቀማጭ ገንዘብን በማሳደግ ተጠቃሚ ደንበኞችን በማፍራት የመንቀሳቀሻ ገንዘብን በማሳደግ ረገድ አመርቂ ስራ መስራቱንም ነው ያስታወቀው፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን እያደረገ ያለውን ተሳትፎ እያጠናከረ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል፡፡
በቀጣይም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚያደርገውን እንቅስቃሴና ቅርጫፎችን ለማሳደግ ጠንክሮ እንደሚሰራ ማስታወቁን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!