Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በሚዛን አማን 24ኛ ቅርንጫፉን ከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በሚዛን አማን ከተማ 24ኛ ቅርንጫፉን ከፈተ፡፡
ቅርንጫፉን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ብሔር፥ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የግብርና ቢሮ ሐላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ መርቀው ከፍተዋል፡፡
የዞኑ አስተዳደር በደቡብ ብሔር፥ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ በቤንች ሸኮ ዞን፣ ሚዛን አማን ቅርንጫፍ መገልገያ የሚሆን 40 ሺህ ኩንታል የሚይዝ መጋዘንና የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚቻልበትን ቢሮ ለሥራ አመቺ እንዲሆን በማድረግ አዘጋጅቷል፡፡
ቅርንጫፉ የምርት ጥራት መመርመሪያ ላቦራቶሪና የተሟላ የቢሮ አደረጃጀት አለው ተብሏል።
በዚህ ቅርንጫፍ በቤንች ሸኮ ዞን ለሚገኙ ስምንት ወረዳዎችና በምዕራብ ኦሞ ዞን ለሚገኙ ሰባት ወረዳዎች አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷል ነው የተባለው።
በሁለቱ ዞኖች የሚገኙ አርሶአደሮችና አቅራቢዎች ያመርቱትን ቡና በአቅራቢያ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ ለመውሰድ የሚያደርጉትን ተጨማሪ ጉዞ በአማካይ በ120 ኪሎሜትር ይቀንሳል ተብሏል፡፡
አከባቢው ከቡና በተጨማሪ ምርት ገበያው የሚያገበያያቸውና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ሰሊጥ፣ አረንጓዴ ማሾ፣ ቅመማ ቅመምና ሌሎችም የግብርና ምርቶች የሚመረቱበት በመሆኑ ቅርንጫፉ እነዚህንም ተቀብሎ ለማስተናገድ ይችላል መባሉ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version