አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅድመና ድህረ ምርጫ ወቅት የሚያጋጥሙ ግጭቶችን ለማስቀረት ዜጎች የማይተካ ሚና እንዳላቸው መዘንጋት የለበትም አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲወለድ የዜጎች ንቁ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።
እንዲሁም በተለይ በምርጫ ወቅት ዜጎች በልዩ ልዩ መንገዶች ተሳትፎአቸውን ሊያረጋግጡ እንደሚችሉም ጠቅሰዋል።
ካርድ ወስደው በሰላማዊ መንገድ ለመምረጥ ራስን ከማዘጋጀት በዘለለ፣ በሲቪክ ማኅበራት አማካኝነት የምርጫው ሂደት ግልጽና ተአማኒ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካርድ አሰጣጡ ዙሪያ፣ የምርጫ ቅስቀሳን በተመለከተ እና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ በምሳሌነት አንስተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!