Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሶሪያ ስደተኞች ጋር የረመዳን ኢፍጣር ማዕድ ተጋሩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሶሪያ ስደተኞች ጋር የረመዳን ኢፍጣር ማዕድ ተጋሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጋጣሚው “ገና በኢስላም ማለዳ ቀናት አያቶቻችን የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የቅርብ ዘመዶችና ሶሃቦችን ተቀብለው ያስተናገዱበትን አንፀባራቂ ታሪክ የሚያስታውስ ነው” ሲሉ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

“በዚህ ድንቅና ውብ ታሪካችን እንደምኮራው ሁሉ፤ ሕዝባችን በተለይም በወጣቱ ትውልድ ውስጥ ለተቸገሩ፣ ለተሰደዱና ጎዳና ላይ ለወደቁ የሰብአዊነትና የእምነት ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ትኩረት እንዲሰጡ እንሻለንም” ብለዋል፡፡

“ይህ ሁኔታ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዛሬም ወደፊትም ከሙስሊም ሀገራትና ሕዝቦች ጋር በወዳጅነት፣ በፍቅርና በሰላም ለመኖር ያለንን ጠንካራ ፍላጎትና እምነት የሚያጸና ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

Exit mobile version