አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ /ፎርማጆ/ የሥልጣን ዘመን መራዘምን ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት በሞቃዲሾ ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል፡፡
ግጭቱ የተቀሰቀሰው ፕሬዚዳንቱን በሚደግፉና በሚቃወሙ የተለያዩ የጸጥታ ኃይሎች መካከል ነው ተብሏል፡፡
ከቤተመንግስቱ አቅራቢያም ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ በሞርታር የታገዘ ተኩስ መሰማቱም ተገልጿል፡፡
ሞቃዲሾ የተነሳው ግጭት ወደ ተለያዩ ከተሞች እየተዛመተ እንደሚገኝ ቢቢሲ በሀገሪቱ የሚገኙ ሚዲያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የፕሬዚዳንቱ የስልጣን ዘመን ባለፈው የካቲት ወር ቢጠናቀቅም በሁለት ዓመት እንደተራዘመ የሚታወስ ነው፡፡
ይህንንም ተከትሎም የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ህብረት ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!