Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ነቢል ማሃዲ ከደቡብ ሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ነቢል ማሃዲ ከደቡብ ሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር አንጀሊና ቴኒይ ጋር በሁለትዮሽና በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ትግበራ ጽኑ አቋም አላት ብለዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት የሚያስተሳስሩ መሰረተ ልማቶች ግንባታ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ነው ያስረዱት፡፡

በተጨማሪም በህዳሴ ግድቡ፣ ስለ ትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስለኢትዮ-ሱዳን ድንበር እና ስለ መጪው ምርጫ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሯ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ ከሰላምና ጸጥታ ጋር በተያያዘ ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ያደረገችውን ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቀጠናውና ከቀጠናው ባሻገር ለሰላምና መረጋጋት የምታበረክተውን አስተዋጽዖ ጉልህ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያን አለመረጋጋት መስማት አንፈልግም ብለዋል፡፡

ከትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ጋር በተያያዘም የውስጥ ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ የውጭ ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

በህዳሴ ግድቡ ዙሪያም የአፍሪካውያን ችግር በአፍሪካውያን መፍትሔ በሚለው መርህ መሰረት የአፍሪካ ህብረት ባስቀመጣቸው መርሆዎች ላይ ተንተርሶ ድርድሩ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Exit mobile version