አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 25 ቀናት ሲካሄድ በቆየው የማህበር ቤት ምዝገባ 12 ሺህ 609 ቤት ፈላጊዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው ከመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየውን የማህበር ቤት ምዝገባ መጠናቀቁንም ቢሮው ገልጿል፡፡
ቢሮው በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ከተመዘገቡት ቤት ፈላጊዎች አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ነዋሪዎች በጋራ ሕንፃ መኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበር በማደራጀት የራሳቸውን ቤት እንዲገነቡ ምዝገባ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል።
በምዝገባ ሂደትም ችግር የገጠማቸው ተመዝጋቢዎች ካሉ ቅሬታቸውን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለቢሮ ማቅረብ እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!