በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 9 ቢሊየን ለማግኘት ታቀዶ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር መገኘቱ ተገለፀ፡፡
የወጪ ንግድ ገቢ አፈፃፀሙ ከተያዘዉ ዕቅድ አንፃር 84 በመቶ ሲሆን ከ2012 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ17 በመቶ ብልጫ አለው ነው የተባለው፡፡
በዚህም በዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙ በግብርና 84 በመቶ ፣ በኢንዱስትሪ 72 በመቶ፣ በማዕድን ዘርፍ 95 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል፡፡
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ክትትል ከሚደረግባቸው የግብርና ምርቶች 674 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 745 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ክትትል ከሚደረግባቸው የግብርና ምርቶች በበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ከዕቅድ አንፃር 110 በመቶ ሲሆን ከ2012 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ 46 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ብልጫ አሳይቷል መባሉን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!