የሀገር ውስጥ ዜና

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሶስት ምክትል ፕሬዚዳንቶቹን ከስራ አገደ

By Tibebu Kebede

January 17, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሶስት ምክትል ፕሬዚዳንቶቹን ከስራ ማገዱን አስታወቀ።

በዩኒቨርሲቲው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተፈራ አስናቀ ሶስቱ ምክትል ፕሬዚዳንቶች የታገዱት በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ውሳኔ መሰረት መሆኑን ተናግረዋል።

የመታገዳቸው ዝርዝር ምክንያት ለጊዜው አለመገለጹን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ዩኒቨርሲቲው ካለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ጀምሮ በመማር ማስተማር ስራው ላይ አለመረጋጋት ገጥሞት መቆየቱ ይታወቃል።