የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ባለፉት 9 ወራት ከ32 ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

By Abrham Fekede

April 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመዲናዋ ባለፉት 9 ወራት 32 ነጥብ 31 ቢሊየን ብር ከገቢ ግብር መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግብራቸውን በአግባቡ ለከፈሉ 178 ግብር ከፋዮች ዕውቅና አበርክቷል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ግብር ከፋዮቻችን ዛሬ የምናመስግናችሁ የአገርን የኢኮኖሚ ስብራት የምትጠግኑ ከመሆናችሁም በላይ መንግሥት ህግን ለማስከበር እያደረገ ላለው ጥረት የጀርባ አጥንት በመሆናችሁ ጭምር ነው ብለዋል።

ግብር ከፋዮችን አላግባብ ከመኮርኮም፣ ከመንቀፍ እና ከማሳደድ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ግብር መክፈልን ለማበረታታት የከተማ አስተዳደሩ ያላግባብ እና በተለያየ ምክንያት መክፈል ያልቻሉ ግብር ከፋዮችን ጉዳይ አጢኖ 6ሺህ 700 የክስ ፋይሎችን በመዝጋት ከ10 ቢሊየን ብር በላይ  መሰረዙን አስታውሰዋል።

የባለፉት 9 ወራት ክንውን ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ14 በመቶ ብልጫ እንዳለው ምክትል ከንቲባዋ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!