አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በኦክስጅን እጥረት ሳቢያ ታካሚዎችን ለመርዳት እየተቸገረ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በተጨማሪም በሆስፒታሉ ያጋጠመውን የኦክስጅን አጥረት ተከትሎ ቀደም ሲል ለሌሎች ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አቅርቦት ማቋረጡንም ነው የገለጸው።
በሆስፒታሉ የፋሲሊቲ መሃንዲስ አቶ ሰለሞን ሸዋንግዛው በአሁኑ ወቅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየተባባሰና የታማሚዎች ቁጥርም እያሻቀበ በመምጣቱ ለኦክስጅን ፈላጊ ታካሚዎች ፈተና ሆኗል ነው ያሉት፡፡
እጥረቱን ለመፍታት በማዕከሉ 24 ሰዓት እየተሰራ ቢሆንም ችግሩን ማቃለል አዳጋች መሆኑን ጠቁመዋል።
ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎችን ፈጽሞ ማከም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ነው ያስረዱት።
የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ ማህበረሰቡ የኮቪድ-19 ተጋላጭነትን ለመቀነስ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰባቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!