Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ314 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ 19 ሲያዙ ስርጭቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ እየተነገረ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ 314 ሺህ 835 ሰዎች በ24 ሰዓታት ውስጥ ኮቪድ 19 እንደተገኘባቸው የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሀገሪቱ ከየትኛውም የዓለም ክፍል በተለየ ሁኔታ ወረርሽኙ እየተስፋፋ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ባለፉት ሰባት ተከታታይ ቀናትም በየዕለቱ ከ200 ሺህ ሰው በላይ በወረርሽኙ እየተያዘ ይገኛል፡፡

ከዚህ ቀደም ህንድ በወረርሽኙ አማካኝነት በአንጻራዊነት አነስተኛ የሟቾች ቁጥር ስታስተናግድ ቆይታለች፡፡

ሆኖም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ነው የተገለጸው፡፡

በ24 ሰዓታት ውስጥም 2 ሺህ 104 ሰዎች ለሕልፈት ተዳርገዋል፡፡

በሀገሪቱ እያጋጠመ ያለው የሖስፒታል አልጋና የኦክስጅን እጥረት ሁኔታውን አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳደረሰው እየተነገረ ይገኛል፡፡

የደልሂ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከኦክስጅን አቅርቦት ጋር በተያያዘ ማዕከላዊ መንግስትን ወቅሷል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version