Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ከኪፕቾጌ ጋር ይፎካከራል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀነኒሳ በቀለ ሚያዚያ ወር ላይ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን ከኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ ጋር እንደሚሮጥ አስታወቀ።

ቀነኒሳ ከኪፕቾጌ ጋር ዳግም ለመወዳደር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

ውድድሩን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየትም በውድድሩ የተሻለ ነገር ለማድረግ ጥሩ መስራ መስራቱንም ነው የተናገረው።

ጉዳት ባለፉት አመታት በማራቶን ያሰበውን እንዳያሳካ እንዳደረገውም ገልጿል።

በውድደሩ ላይ በማራቶን ፈጣን ሰዓት ያላቸው ስምንት አትሌቶች ይወዳዳሩ ተብሏል።

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ሞስነት ገረመው እና ሙሌ ዋሲሁን ከቀነኒሳ ጋር በለንደን ጎዳናዎች አብሮው የሚሮጡ ይሆናል።

የለንደን ማራቶን አዘጋጆችም ዓለም የብርቱዎችን ፉክክር ለማየት በጉጉት እየጠበቀ ነው ብለዋል።

ቀነኒሳ በ2019 የበርሊን ማራቶንን 2 ሰዓት ከ01 ደቂቃ 41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቡ ይታወሳል።

የርቀቱ ክብረ ወሰን ባለቤት ኤሉድ ኪፕቾጌ በኦስትሪያ ቪየና ማራቶንን ከ2 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በመግባት የመጀመሪያው ሰው ሆኗል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Exit mobile version