አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚደረጉ የእግር ኳስ ውድድሮችን ለመምራት መመረጣቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን አስታወቀ።
ፌዴሬሽኑ የተወሰኑ ወራት በቀሩት የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ተሰላፊ የሆነችው ኢትዮጵያ ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በእግር ኳስ ዳኝነት በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ትወከላለች ብሏል።
ፊፋ በዛሬው እለት ባሳወቀው የዳኞች ዝርዝር በቶክዮ ኦሎምፒክ የሚደረጉ የእግር ኳስ ውድድሮችን እንዲመሩ ከመረጣቸው ዋና ዳኞች መካከል ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ አንዱ ሆኖ መመረጣቸውን ፌዴሬሽኑ በፌስቡክ ገፁ ላይ አስፍሯል።
ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማም “ሁሌም ስጠብቀው እና ሳልመው በነበረው የኦሎምፒክ ውድድር ላይ ሀገሬን በእግር ኳስ ዘርፍ በዳኝነት በመወከሌ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል” ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!