የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ ተቋማዊ ሪፎርም እያደረገ መሆኑን ገለጸ

By Meseret Awoke

April 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህገመንግስታዊ ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት ተቋማዊ ሪፎርም እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ተቋማዊ ሪፎርሙን በተመለከተ ምክር ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ይገኛል፡፡

ሪፎርሙ ሀገራዊ አንድነትና ዘላቂ ሰላም መገንባት፣ ውጤታማ ሽግግርና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ማረጋገጥ፣ የህገ መንግስት የበላይነትና ህገ- መንግስታዊነትን ማረጋገጥ እንዲሁም ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም መገንባት በሚሉት ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ምክር ቤቱ የህገ መንግስቱ ጠባቂ ተቋም መሆኑን ገልጸው፤ በህገ መንግስት አተረጓጎም ስርዓት መርሆዎችና ሂደት በዝርዝር ባለመደንገጋቸው ምክንያት በተለይም በአቤቱታ አቀራረብ፣ ውሳኔ አሰጣጥና አፈጻጸም ዙሪያ ክፍተት ይስተዋላል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተደረሰው ስምምነትና በተከናወነው የመጀመሪያ ዙር ጥናት ሪፖርት ላይ እየተወያየ ሲሆን፤ በህገ መንግስት የበላይነትና ህገ መንግስታዊነትን ማረጋገጥ ላይ ማተኮሩን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!