አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቶ አለልኝ አድማሱ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ጎብኝተዋል፡፡
አምባሳደሩ የሚዲያ ተቋሙን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
በገለፃቸው ፋና ከተቋቋመ ጀምሮ ህብረተሰቡን በማዝናናት በማስተማር እንዲሁም ህዝቡን ከመንግስት አካል ጋር በቀጥታ በማገናኘት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡
በቴሌቪዥን፣ በራዲዮ እና በዲጅታል ሚዲያውን አማራጮች ለህዝቡ እያደረሰ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ አድማሱ ሚዲያው በሰለጠነ የሰው ሃይል፣ በአዲስና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቶ አለልኝ አድማሱ በበኩላቸው፣ እስራኤል እና ኢትዮጵያ ያላቸውን የቆየ ወዳጅነት አንስተው ወደፊትም ሁለቱን ሃገራት በተለያየየ ዘርፎች ይበልጥ በማስተሳሰር ረገድ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ፋና በብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በተለይ በዩትዩብ ቻናሉ በሚያስተላልፋቸው ፕሮግራሞቹ በእስራኤል ማህበረሰብ ዘንድ ተወዳጅ ሚዲያ ነው ብለዋል፡፡
ፋና ትክክለኛ መረጃን ለማህበረሰቡ በማድረስ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ኤምባሲው ከፋና ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ይሰራል ነው ያሉት፡፡
በፌቨን ቢሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!