Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኮሚሽነር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኮሚሽነር ያኔዝ ሌናርቺች ጋር መከሩ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በክልሉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው አሁንም ቢሆን ተግዳሮቶች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡
 
በክልሉ የተለዩ ችግሮችንም ለመቅረፍ የመንግስትን ዝግጁነት አረጋግጠዋል፡፡
 
የአውሮፓ ህብረት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኮሚሽነር በበኩላቸው በክልሉ እየተሻሻለ ስለመጣው ሰብዓዊ አቅርቦት አበረታተዋል፡፡

እንዲሁም በክልሉ ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሰብዓብዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋራ ለመመርመር የደረሱትን ስምምነት አድንቀዋል፡፡

በተጨማሪም የኤርትራ ወታደሮች ከክልሉ እንዲወጡ የተወሰደው ውሳኔም የሚበረታታ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ በበኩላቸው በክልሉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው አሁንም ቢሆን ተግዳሮቶች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

በክልሉ የተለዩ ችግሮችንም ለመቅረፍ የመንግስትን ዝግጁነት አረጋግጠዋል፡፡

ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በበኩላቸው አብዛኞቹ የእርዳታ ድርጅቶች መቀሌ ላይ ብቻ እንደተገደቡ ተናግረዋል፡፡

የእርዳታ ድርጅቶቹ በክልሉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች እስካሁን ከተደረገው ድጋፍ 7 በመቶ ምግብ ነክ ያልሆኑ እና 30 በመቶ ምግብ ነክ ድጋፎችን እንደሚሸፍኑ ገልጸዋል፡፡

አቶ ምትኩ አብዛኛው ድጋፍ መንግስት እየሸፈነ እንደሚገኝም አስታውሰዋል፡፡

በተጨማሪም ባለፉት አስራ አምስት ቀናት ተደራሽ ያልነበሩ ስድስት ወረዳዎችም በጸጥታ አካላት ትብብር መድረስ እንተቻለ መናገራቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version