የሀገር ውስጥ ዜና

የሕዳሴ ግድብ ሁለት የውሃ ማስተንፈሻዎች ተጠናቅቀው ስራ ጀመሩ

By Meseret Demissu

April 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የሕዳሴ ግድብ ሁለት የውሃ ማስተንፈሻዎች ተጠናቅቀው ስራ መጀመራቸውን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ገለጹ፡፡

ሁለቱ ማስተንፈሻዎች አጠቃላይ ዓመታዊውን የዓባይ ፍሰት የማሳለፍ አቅም እንዳላቸው ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ማስተንፈሻዎች በግድቡ ሙሌት ወቅት የዓባይ ውሃ ወደ ታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ያለውን ፍሰት እንዲጨምር የሚያስችሉ ናቸውም ነው ያሉት።

ሚኒስትሩ አያይዘውም በዚህም ወደ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት የሚኖረውን የውሃ ፍሰት እንደማያስተጓጎል ማረጋገጫ መሆኑን አንስተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!