የሀገር ውስጥ ዜና

የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ የመንግስት ግዴታ ነው_ የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ

By Tibebu Kebede

April 18, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)- መማክርት ጉባኤው እየተፈጸሙ ያሉ ተከታታይና የተቀናጁ ጥቃቶችን በፅኑ አወገዞ በህይወት እና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት እጅጉን ያዘነ መሆኑን ገልጿል።

የአማራ ክልልም ሆነ የፌዴራል መንግስት በዚህ ተግባር በቀጥታ ተሳታፊ በሆኑት እና ጥቃት አቀናባሪዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ መማክርቱ አሳስቧል።

በሰሜን ሸዋ በተለይም በአጣዬ ፣ በካራ ቆሪ፣ በሸዋ ሮቢት፣ማጀቴ፣አለላ፣አንጾኪያ እና አካባቢው የዜጎች ደህንነት የማስጠበቅ የቅድሚያ ግዴታ የመንግስት መሆኑን በማስገንዘብ የክልሉ እና የፌዴራል መንግስት ይህን ግዴታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!