የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋን የልዑካን ቡድን ተቀበሉ

By Tibebu Kebede

April 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የተላከውንና በአምባሳደር ክዋሜ ታፒዋ ሙዛዋዚ የሚመራውን ልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ልዑካኑ ያለፉት 500 ዓመታት የአፍሪካ ትክክለኛው ታሪክ እንዲመዘገብ የአፍሪካ ሕብረት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት፥ የተዘጋጀውን “አፍሪካን ፋክት ቡክ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ አበርክተውላቸዋል።

የአጀንዳ 2063 እጅግ ጠቃሚ አካል የሆነው ይህ የእውነታዎች ስብስብ፥ የአፍሪካን ባህል፣ ታሪክና ትውፊት ለዓለም የሚያስተዋውቅ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ልዑካኑ ይህንን መጽሐፍ  በማበርከት ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነጻነት የተጫወተችውን አይተኬ ሚና እና ለፓን-አፍሪካዊነት የምታደርገውን ቀጣይ ድጋፍ በማድነቅ ዕውቅና ሰጥተዋል።ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን