የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከክልል ፕሬዚዳንቶችና ከምርጫ ቦርድ አመራሮች ጋር በምርጫ ዙሪያ ተወያዩ

By Abrham Fekede

April 15, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከክልል ፕሬዚዳንቶችና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አመራሮች ጋር  በምርጫ ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ከምርጫ ጋር በተያያዘ  ከዚህ ቀደም በየካቲት ወር የበይነ መረብ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

በዛሬ ውይይት የምርጫ ክንውኖችን እና ተግዳሮቶችን ለመገምገም በድጋሚ መገናኘታቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጁነት በአጥጋቢ ሁኔታ መከናወኑን ለማረጋገጥና መራጮች በቀሪው ጊዜ እንዲመዘገቡ ለማስቻል አቅጣጫዎችን መቀመጣቸውንም ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም ዜጎች በቀጣይ ቀናት የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ አበረታታለሁ ብለዋል።

6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊነት ማረጋገጥ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉም ነው ያሳሰቡት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን