የሀገር ውስጥ ዜና

ዜጎች የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጠበቃል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

By Meseret Awoke

April 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ዜጎች የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሊከናወን ጥቂት ሳምንታት ብቻ ቀርተውታል ያሉ ሲሆን፤ በሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 38 ሁሉም ኢትዮጵያዊ የመምረጥና የመመረጥ መብት እንደሚደነግግ ገልጸዋል።

የሀገራችንን የነገ ዴሞክራሲ ለመወሰን፣ ዛሬ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ እናውጣ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ካርድ ለማውጣት ነገ አትበሉ፤ ነገ ከዛሬ ይጀምራል ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን